- October 5, 2021
- Posted by: admin
- Category: Uncategorized
No Comments
ኩባንያችን የባለሙያዎችን እውቀትና ሙያዊ ክህሎት ለማሳደግ በየዓመቱ የረዥምና የአጭር ጊዜ ስልጠናዎችን ይሰጣል፡፡
በመሆኑም በግንባታ ፕሮጀክቶቻችን አፈጻጸም ላይ የሚታዩ የክህሎት ክፍተቶችን ለመቅረፍ ብቁና የተሻሉ የምህንድስና ባለሙያዎችን ለማፍራት የሚያስችሉ በርካታ አጫጭር የስልጠና ርእሶችን በመለየት ተገቢውን እውቀትና ክህሎት የሚያስጨብጡ አሰልጣኞችን በማወዳደርና በመለየት በቀን 24/24/2014 ዓ.ም የስልጠና ፕሮግራሙ ተጀምሯል፡፡
በዚህም በመጀመሪያ ቀናት በዋተር ካድ (WaterCad) የስልጠና ርእስ የተጀመረ ሲሆን በቀጣይም Civil 3D, Premavera P6 እንዲሁም የኤሌክትሮ መካኒካል እቃዎች ተከላና የሶላር ሴስተም ስልጠናዎች በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ ለመስጠት የቅድመ-ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀዋል፡፡