በተለያዩ የስራ ክፍሎች በተናጠል ሲደረጉ የቆዩ የስራ አፈጻጸም ግምገማዎች ተጠናቀቁ፡፡

ከነሃሴ ወር 2012 ዓ.ም አጋማሽ ጀምሮ በኩባንያችን ሲደረጉ የነበሩ በ2020 በጀት ዓመት የሰባት ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረኮችን ተጠናቀዋል፡፡ የኮሮና ወርረሽኝን ለመከካከል ሲባል በጋራ ይደረግ የነበረውን ዓመታዊ የስራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በተመጠነ የሰው ቁጥር በስራ ክፍል ደረጃ በተዘጋጁ የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶችና እያጋጠሙን ባሉ  ችግሮች ዙሪያ ውይይትና ግምገማ ተገደርጓል፡፡  በዚህም ሰራተኛው ጥንካሬዎችን ይበልጥ የሚያጎለብትበትና  በአመለካከት፤በአሰራርና በክህሎት የታዩ ክፍተቶችን በሚሞላ አግባብ ራሱን ያየበትና እንዲሁም ሃሳብን በተሻለ ሁኔታ መግለጽ የተቻለበትና እርስ በርስ ለመመማርም እድል የፈጠሩ የውይይት መድረኮች እንደነበሩ በተግባር ታይቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሰራተኛው የሚጠይቃቸውን ጥያቄዎች ከወቅቱ ነባራዊ ሁኔታ አንጻር በማየት የኩባንያውን አቅም ግምት ውስጥ ያስገባና አሰራርን ተከትሎ ሊፈቱ በሚችሉ ችግሮች  ዙሪያ መግባባት የተደረሰ ሲሆን በእያንዳንዱ የግምገማ መድረክ የስራ ሃላፊዎች በመገኘት ምላሽና ማብራሪያ እንዲሰጡበት መደረጉም ከመመሪያና አሰራር አኳያ ይበልጥ ግልጽ መሆን ያለባቸውን ጉዳዮች ማስረዳት የተቻለበት አጋጠሚ ነበር፡፡

በአጠቃላይ በሁሉም የግምገማ መድረኮች ሰራተኛው የተሰማውን ሃሳብ በግልጽ ማውጣት የተቻለበት፤ የኩባንያውን ነባራዊ ሁኔታና ተግዳሮቶች በመረዳት ችግሮችን በጋራ በመፍታት ለቀጣይ ስራ ውጤታማ መሆን ራሱን ያነሳሳበት እና አመራሩና ሰራተኛው እየገጠሙ ያሉ ውጫዊ ችግሮችን ተቋቁሞ የተሻለ መፈጸምና የኩባንያውን እድገት ለማስቀጠል በጋራ መረባረብ እንደሚገባ አቅጣጫ የተሰጠባቸው መድረኮች ሆነው ተጠናቀዋል፡፡Leave a Reply