በኩባንያችን ተገንብቶ የተጠናቀቀው የድድገመኝ የቀበሌዎች አገናኝ መጠጥ ውሃ ግንባታ ፕሮጀክት ተመረቀ።

በደቡብ ጎንደር ዞን አንዳቤት ወረዳ ሦስት የገጠርና አንድ የከትማ ቀበሌዎችን በማገናኜት 19‚300 የህብረተሰብ ክፍልን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ያደረገውና በኩባንያችን ተገንብቶ የተጠናቀቀው የድድገመኝ የቀበሌዎች አገናኝ መጠጥ ውሃ ግንባታ ፕሮጀክት የአብክመ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና ሌሎች የክልልና የዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ሐምሌ 23/2012 ዓ•ም ተመረቀ።

ፕሮጀክቱ 3 የተለያዩ የውሃ መጠን የመያዝ አቅም ያላቸው የውሃ ጋኖች፣ 11•9 ኪ/ሜ የግፊት መስመር፣ 47•2 ኪ/ሜ የስርጭት መስመር ዝርጋታ፣ 45 የውሃ ማደያ ቦኖዎች እና 15 ፎሴትችን የያዘ ነው። ከዚህ በተጨማሪም በሰከንድ 20 ሊትር ውሃ የመግፋት አቅም ያለው ጠላቂ ፓምፕ፣ እያንዳንዳቸው በሰከንድ 10 ሊትር ውሃ የመግፋት አቅም ያላቸው 3 ሰርፌስ ፓምፖችና ባለ 280 KVA ጀነሬተር ተገጥሞለታል።Leave a Reply