- August 26, 2021
- Posted by: admin
- Category: Uncategorized
No Comments

የኩባንያችን አመራሮችና ሰራተኞች በተለያዩ አውደ ውጊያዎች ላይ ለሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት፤ ልዩ ሃይል እና ፋኖ ቀደም ብሎ የተጀመረውን የገንዘብ ድጋፍ በአዲስ መልክ በማጠናከር የአንድ ወር ሙሉ ደመዎዝ ከ1.6 ሚልዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጋቸው ይታዎቃል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ኩባንያችን የ2.8 ሚልዮን ብር የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ እና ለህልውና ዘመቻው አገልግሎት የተለያዩ ቀላልና ከባድ ተሸከርካሪዎች እንዲሁም የሎጅስቲክስ ድጋፍ በማድረግ የበኩሉን ሚና እየተወጣ ይገኛል፡፡
በዛሬው ዕለትም ( ነሃሴ-19/2013 ዓ.ም) በኩባንያችን ቅጥር ግቢ በመገኘት የደም ልገሳ ፕሮግራም በማካሄድ የዜግነት ግዴታችውን በመወጣት ለህልውና ዘመቻው አጋርነታቸን አሳይተዋል፡፡

