- March 7, 2021
- Posted by: admin
- Category: Uncategorized
No Comments
ኩባንያችን በብር 266 ሚልዮን የሚገነባቸው የደብረ ማርቆስ ከተማና የስናን ወረዳ ረቡዕ ገበያ መጠጥ ውሃ ግንባታ ፕሮጀክቶች በይፋ ተጀምረዋል። ፕሮጀክቱን የኩባንያችን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ በላይ ጫኔ፣ የአብክመ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጥላሁን መሃሪ፣ የአብክመ ውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ማማሩ አያሌው እና የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አያሌው አስጀምረዋል።
ፕሮጀክቱ በደብረ ማርቆስ ከተማ የሚገነባ 5000 ሜ/ኩ ውሃ የመያዝ አቅም ያለው እና 200 ሜ/ኩ ውሃ የመያዝ አቅም ያለው የውሃ ማጠራቀሚያ ጋኖች፣ ከውሃ መገኛው(ሰንተራ) እስከ ደብረ ማርቆስ ከተማ የሚዘረጋ 7 ኪ/ሜ እና ከሰንተራ እስከ ረቡዕ ገበያ የሚዘረጋ 34 ኪ/ሜ የግፊት መስመር፣ 5 የፓምፕና ጀነረተር ቤቶች፣ የተለያየ መጠን ያላቸው 4 ቡስተር ስቴሽኖች ግንባታና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራዎችን ያካተተ ነው።በዞኑ ከዚህ በፊት በተለያዩ ምክንያቶች በግል ኮንትራክተሮች ተጀምረው ሳይጠናቀቁ የቆዩና ኩባንያችን ተረክቦ በማጠናቀቅ ለህዝብ አገልግሎት ያበቃቸውን ጨምሮ 12 ፕሮጀክቶችን አጠናቀን ለአገልግሎት ማብቃታችን የሚታዎስ ነው።
(የሽፋን ምስሉ ከአብመድ የተወሰደ)