- September 23, 2020
- Posted by: admin
- Category: Uncategorized
No Comments
የገቢዎች ሚኒሰቴር የታማኝ ግብር ከፋዮች ሽልማትና ዕውቅና ሰጥቷል።ተሸላሚዎቹ ከሀገር ውስጥ ታክስና ከጉምሩክ ቅርጫፎች የተመረጡ ናቸው፡፡
በዚህ በቤተመንግስት በተዘጋጀው በዚህ 2ኛው ዙር የፌዴራል ግብር ከፋዮች ሽልማት ስነ-ስርዓት ላይ ኩባንያችን አንዱ በመሆን የብር ዋንጫ ተሸላሚ ሁኗል። ኩባንያችን ባለፈው ዓመት በተካሄደው የመጀመሪያው ዙር የምስጉን ግብር ከፋዮች ሃገር አቀፍ እውቅና አሰጣጥ ፕሮግራም ላይም ተሸላሚ መሆኑ ይታወሳል።
ታማኝ ግብር ከፋይ በመሆናችን ላገኘነው ለዚህ ሽልማት ጉልህ ሚና የነበራችሁ የኩባንያችን ሰራተኞቻችንና አመራሮች እንዲሁም ባለድርሻ አካላትን ለማመስገን እንወዳለን። ለአገራችን የሚጠበቅብንን አስተዋጽዖ ለማበርከት በቀጣይም ተግተን እንሰራለን።