- April 13, 2022
- Posted by: admin
- Category: Uncategorized
No Comments
ኩባንያችን ጢስ እሳት ውኃ ሥራዎች ኃ/የተ/የግ/ማ በቅርቡ ከጣሊያን ባስመጣው ዘመናዊ ሪግ በዋና ቢሯችን ግቢ ውስጥ 200 ሜ ጥልቀት ያለው የከርሰ ምድር ውኃ ቁፋሮ በተሳካ ሁኔታ በማካሄድ የንፁህ መጠጥ ውኃ አበልፅጓል። ይህንን ንፁህ መጠጥ ውኃም ከባህርዳር ከተማ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጋር በመነጋገር፣ አገልግሎቱ የመስመር ዝርጋታ አካሂዶ፥ በኩባንያችን የኤሌክትሪክ ኃይል እና ፓምፕ በመጠቀም ለአፄ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ ነዋሪ ለሆኑ 10,000 ማኅበረሰብ ንፁህ የመጠጥ ውኃ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓል። በዚህም የባህርዳር ከተማ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ከፍተኛ ምስጋና አቅርቧል።ኩባንያችን ከዚህ በፊትም በተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶች በመሳተፍ የበኩሉን ድርሻ በመወጣት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል።