ኩባንያችን እውቅና ተሰጠው
- July 22, 2019
- Posted by: admin
- Category: Uncategorized
No Comments
ኩባንያው በተሰማራባቸው የውኃ ዘርፍ ተግባራት የህብረተሰቡን የመጠጥ ውኃ አቅርት ችግሮች ከመፍታት በተጨማሪ አነስተኛና መካከለኛ የመስኖ አውታር ዝርጋታ ፕሮጀክቶችን በጥራት በማከናወን የክልሉን ልማት በማፋጠን ላይ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በየዓመቱ ያስገመዘበውን ትርፍ በታማኝነት ለሚመለከተው ገቢ ሰብሳቢ መ/ቤት በማሳወቅና በወቅቱም በመክፈል እንደተቋም ሀገራዊ ግዴታውን እየተወጣ ይገኛል፡፡
ይህንን መነሻ በማድረግ ሃምሌ 15/2011 ዓ.ም የገቢዎች ሚኒስቴር ባዘጋጀው የምስጉን ግብር ከፋዮች ሃገር አቀፍ እውቅና አሰጣጥ ፕሮግራም ላይ ኩባንያችን በሲሊቨር ደረጃ እውቅና ተሰጥቶታል፡፡ ይህንን የምስጉን ግብር ከፋይ እውቅና ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እጅ የተቀበልን ሲሆን መላው የኩባንያው ሰራተኞችና አመራሮችና ላረጋችሁት ጥረት ኩባንያው ከፍ ያለ ምስጋና ያቀርባል፡፡