ኩባንያችን ከኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ጋር የአቅም ግንባታ መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡

ኩባንያችን ጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ኃ/የተ/የግል ማህበር በጥራት ሽልማት ውድድር ያለንን ተሳትፎ ይበልጥ ለማሳደግና ወደ ልህቀት ለመሸጋገር የሚያደርገውን ጥረት ለመደገፍ በተለያዩ ርእሶች ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠናና ሙያዊ ድጋፎችን ለማድረግ የሚያስችል የጋራ መግባቢያ ሰነድ በጋፋት ኢንዶውመንት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሽመልስ በላቸውና በኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ቴወድሮስ መብራቱ የፊርማ ስነ-ስርዓት ተካሄዷል፡፡
በጋራ መግባቢያ ሰነዱም የልቦና ውቅር ለውጥ፤ የፕሮጀክት ስራ አመራር ከልህቀት ሞዴል አንጻር፤ ተቋማዊ ልህቀት፤ አመራርና ተከታይ ያላቸው ተዛምዶ፤ የጥራት ጽንሰ ሃሳብ እና ማሳያዎች እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ጽንሰ ሃሳብና ማሳያዎች ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎች ተካተዋል፡፡Leave a Reply