- May 29, 2020
- Posted by: admin
- Category: Uncategorized
No Comments
ኩባንያችን ጢስ እሳት ውኃ ስራዎች በሃገራችን እየተስፋፋ የመጣውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በስራ ቦታ በመከላከልና የጥንቃቄ እርምጃዎች በመውሰድ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ሰራተኛው ራሱን ከወረርሽኙ ይጠብቅ ዘንድ የተለያዩ ጽሁፎች በማሰራጨት፤ በግልና በጋራ የምንገለገልባቸውን የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በማሟላትና በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውሉ በመከታተል፤የካፍቴሪያ መስተንግዶ አገልግሎት አጋላጭነት በመቀነስ፤ የትራንስፖርት ሰርቪስ ተሽከርካሪዎችን በማመቻቸት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ጥረት ተደርጓል፡፡
ይህንን ጥረት ወደ ግንባታ ፕሮጀክቶቻችን ለማስፋት በየግንባታ ሳይቶቹ የተጀማመሩ ስራዎች ያሉ ቢሆንም የመከላከል ስራውን የበለጠ ተግባራዊ ለማድረግ በክልሉ ከተማ ልማትና ቤቶች ኮንስትራክሽን ቢሮ በኩል የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከያ ፕሮቶኮል ወጥቶ ስራ ላይ እንዲውል አባሪ ተደርጎ የተላከልንን መመሪያ ሁሉም ማየት እንዲችል ከዚህ በታች ያስቀመጥን ሲሆን ሁላችንም ይህንን ተግባራዊ በማድረግ አስፈላጊውን የመከላከል እርምጃ መውሰድ ይጠበቅብናል፡፡