ካይዘን ስልጠና

ኩባንያችን የፈጻሚ ሃይሉን አቅምና እውቀት ለማሳደግ በክረምት በርካታ የክህሎት ስልጠናዎችን  በውስጥ አቅምና ከኩባንያው ውጭ ሰፊ ልምድ ያላቸውን አሰልጣኞች በመጋበዝ በየዓመቱ መስጠት ከጀመረ ወዲህ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በያዝነው 2019 (እ.አ.አ) የስራ ዘመንም በየስራ ክፍሉ የተለዩና ለቀጣይ ስምሪት አቅም ሊሆኑ በሚችሉ የስልጠና ርእሶች ዙሪያ ሰፊ ዝግጅት በማድረግ ከኦገስት ወር 2019 (እ.አ.አ) አጋማሽ ጀምሮ ስልጠናዎቹ በተደራጀ መንገድ ይሰጡ ዘንድ ዝርዝር ፕሮግራም ተዘጋጅቷል፡፡ ከዚህ አንጻር በወጣው ፕሮግራም መሰረት በካይዘን አስተባባሪው አማካኝነት የተዘጋጀውን ከይዘን ልማት ቡድን መሪዎችና ጸሃፊዎች ተግባርና ሃላፊነት፤ ቀላል የችግር መፍቻ መሳሪያዎች ምንነትና አጠቃቀም እንዲሁም ስለ ውጤት ቅመራ ለ20 ተሳታፊዎች የ1 ቀን ስልጠና በመስጠት የክረምት ስልጠና ፕሮግራሙ ተጀምሯል፡፡

1 Comment

Leave a Reply

how can we help you?

Contact us at the Consulting WP office nearest to you or submit a business inquiry online.

Looking for a First-Class Consultant?