- May 13, 2020
- Posted by: admin
- Category: Uncategorized
No Comments

የኩባንያችን ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ዘመኑ ዋለልኝ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ስንገልጽ በተሰበረ ልብ ውስጥ ሆነን ነው።
አቶ ዘመኑ ዋለልኝ ከአባታቸው ከቄስ ዋለልኝ ቢሻው እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ላቀች አሰጌ ጥር 5 ቀን 1968 ዓ/ም በምዕራብ ጎጃም ዞን ጃቢ ጥህናን ወረዳ ተወለዱ። ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ሊሻላቸው ባለመቻሉ በተወለዱ በ44 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። አቶ ዘመኑ ዋለልኝ ባለ ትዳርና የአንድ ሴት ልጅ አባት ነበሩ።
በኩባንያችን ዋና ሥራ አስኪያጅ ህልፈተ ህይወት የተሰማንን መሪር ሐዘን እየገለጽን ለመላ የኩባንያችን ሰራተኞች፣ ለቤተሰቦቹና ወዳጅ ዘመዶች በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን።