የንጹህ መጠጥ ውሃ ግንባታ ፕሮጀክቶች የግንባታ ውል ስምምነት በባህር ዳር ከተማ ተካሂዷል።

የአስ ከተማ እና የሰኞ ገበያ መጠጥ ውሃ ግንባታ ፕሮጀክቶች ግንባታ ውል ስምምነት በባህር ዳር ከተማ ከፌደራል ውሃ ልማት ኮሚሽን ጋር ተፈራርመናል። የውል ስምምነቱ የኢፌዴሪ ውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትር ዶ/ር ኢንጅነር ስለሽ በቀለ በተገኙበት በአብከመ ውሃ፣ መስኖና ኢንርጂ ቢሮ ኃላፊ በዶ/ር ማማሩ አያሌው እና በጢስ እሳት ውሃ ሥራዎች ኃ/የተ/የግል ማኅበር ም/ሥራ አስኪያጅ በአቶ በልስቲ አማኑ አማክኝነት የተፈፀመ ነው።ፕሮጀክቶቹ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ጋዝጊብላ ወረዳ እና በሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ የሚተገበሩ ሲሆን በድምሩ ብር 83 ሚልዮን ወጪ ይደረግባቸዋል።

ለፕሮጀክቶቹ ተፈፃሚነት የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ የውኃ ልማት ኮሚሽን እና የአማራ ክልል ውኃ መስኖና ኢነርጂ ቢሮ በጋራ እንደሚሰሩም ዶክተር ኢንጂነር ስለሽ በቀለ ተናግረዋል፡፡



Leave a Reply

This website uses cookies and asks your personal data to enhance your browsing experience. We are committed to protecting your privacy and ensuring your data is handled in compliance with the General Data Protection Regulation (GDPR).