የንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታ ፕሮጀክት የውል ስምምነት ተካሄደ።

ኩባንያችን ከደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ጋር በገባው የውል ስምምነት መሰረት ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብና በአካባቢው ለሚገኙ ለወፍ ዳር መንደር አገናኝ ቀበሌ የንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታ ፕሮጀክት ከቫት ጋር በብር 89,540,697.03 በ12 ወራት ለማጠናቀቅ ወደ ስራ የገባ ሲሆን ዋና ዋና ስራዎቹም የቧንቧ ዝርጋታ፤ መገጣጠሚያና የኤሌክትሮ መካኒካል እቃዎች ተከላና የግንባታ ስራዎች ናቸው፡፡
በሌላ በኩል ከክልሉ ውሃ፤ መስኖና ኢነርጂ ልማት ቢሮ በዋን ዋሽ በጀት የጉድጓድ ቁፋሮ ስራዎችን ያገኘ ሲሆን፤ ደ/ጎንደር ዞን ስማዳና ጉና በጌምድር ወረዳዎች 11 መለስተኛ ጥልቅ ጉድጓዶች፤ ማእከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ-2 ና ላይ አርማጭሆ ወረዳዎች 14 መለስተኛ ጥልቅ ጉድጓዶች፤ ደቡብ ጎንደር ዞን እብናት እና ታች ጋይንት ወረዳዎች 10 መለስተኛ ጥልቅ ጉድጓዶች፤ በአጠቃላይ 35 መለስተኛ ጥልቅ ጉድጓዶች ቫትን ጨምሮ ብር 14,037,455.44 የውል ስምምነት አካሂዷል።Leave a Reply