- August 5, 2020
- Posted by: admin
- Category: Uncategorized
No Comments
ኩባንያችን ከሚያከናውናቸው የኮሮና ወረርሽኝ መከላከል ስራዎች በተጨማሪ ከየስራ ክፍሉ ይበልጥ ለወረርሽኙ ተጋላጭ የሆኑ ተንቀሳቃሽ ሰራተኞችና ከውጭ ደንበኞች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ካላቸው ሰራተኞችና ከስራ ባህሪያቸው አንጻር እንቅስቃሴ የሚበዛባው ሰራተኞችና የስራ መሪዎች በቀን 28/11/2012 ዓ.ም የጤና ባለሙያዎችን በመጋበዝ ኮቪድ -19 ምርመራ ናሙና እንዲወሰድ ተደርጓል፡፡ በዚህም በተጠየቀው 100 ናሙና መሰረት በዋናው ቢሮ የሚሰሩ፤ ከመስክ የተመለሱና በተለያዩ ስራዎች በግቢው ውስጥ የተሰማሩ በድምሩ የ100 ሰራተኞች ናሙና የመሰብሰብ ስራ ተሰርቷል፡፡ ይህም ሰራተኛው ስለ በሽታው ይበልጥ እንዲገነዘብና ራሱንና ቤተሰቡን እንዲጠብቅ የሚያግዝ በመሆኑ ተግባሩ ለሌሎች ተቋማት አርአያነት ያለው ነው፡፡
