የደም ልገሳ
በዛሬው እለት ማለትም ነሃሴ 20/12/2011 ዓ.ም የኩባንያው አመራሮችና ሰራተኞች በበጎ ፈቃደኝነት የደም ልገሳ አድርገዋል፡፡ ከደም ልገሳ ፕሮግራሙ በፊት በእለቱ ለተገኙ የኩባንያው ሰራተኞች ግንዛቤ የተፈጠረላቸው ሲሆን በፈቃደኝነት ደም የመለገስ ስራው ተከናውኗል፡፡ በፕሮግራሙ ተሳታፊ ለሆናችሁና ደም የለገሳችሁ የኩባንያው አመራሮችና ሰራተኞች ለሌሎች ተምሳሌት የሆነ ተግባር የፈጸማችሁ በመሆኑ ኩባንያው ከፍ ያለ ምስጋና ያቀርባል፡፡