የገለሶት የቀበሌዎች አገናኝ መጠጥ ውሃ ግንባታ ፕሮጀክትን ለመገንባት የሚያስችል የውል ስምምነት ተካሄደ።

ታህሳስ 05 ቀን 2013 ዓ/ም የገለሶት የቀበሌዎች አገናኝ መጠጥ ውሃ ግንባታ ፕሮጀክትን ለመገንባት የሚያስችል የውል ስምምነት ከውኃ ልማት ኮሚሽን ጋር ተፈራርመናል። ስምምነቱ የኢፌዴሪ የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ልማት ሚንስትር ዶ/ር ኢንጅነር ስለሽ በቀለ እና የአብክመ ውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ማማሩ አያሌው በተገኙበት በውሃ ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር በዶ/ር በሻህ ሞገሴ እና በጢስ እሳት ውሃ ሥራዎች ኃ/የተ/የግል ማኅበር ዋና ሥራ አስኪያጅ በአቶ በላይ ጫኔ አማካኝነት ነው የተፈጸመው።የገለሶት የቀበሌዎች አገናኝ መጠጥ ውሃ ግንባታ ፕሮጀክት በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ የሚገነባ ፕሮጀክት ሲሆን ፕሮክቱ ሲጠናቀቅ ከ26 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎችን የንጹህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት ተጠቃሚ ያደርጋል። ግንባታው በብር 102 ሚልዮን ውጪ የሚገነባ ሲሆን የአማራ ዲዛይንና ቁጥጥር ስራዎች ድርጅት የማማከር ስራውን ያከናውናል።Leave a Reply