- July 1, 2021
- Posted by: admin
- Category: Uncategorized
No Comments
በደቡብ ጎንደር ዞን ደራና ፎገራ ወረዳዎች ክረምት በገባ ቁጥር ተደጋጋሚ የጎርፍ አደጋ የሚከሰትባቸው አካባቢዎች ናቸው፡፡ የጉማራ ወንዝ መሙላት ለአደጋው መከሰት አንድ ምክንያት መሆኑ ይታወቃል። በተደጋጋሚ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ቀጥተኛ ተጎጂዎች ሆነዋል፤ ሰብል ወድሟል፤ የቤት እንስሳት ሞተዋል፤ ንብረት ለውድመት ተጋልጧል።በያዝነው ዓምት ይህን አደጋ ለመቀነስ ጉማራ ወንዝ ላይ ኩባንያችን የጎርፍ መከላከያ በመስራት ላይ ይገኛል። በዚህም የኩባንያችን ማሽኖች ገብተው እየሰሩ ይገኛሉ፡፡