- April 6, 2022
- Posted by: admin
- Category: Uncategorized
No Comments
በጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ኃ.የተ. የግል ኩባንያ እና በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንሰቲትዩት መካከል በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈርሟል፡፡ የመግባቢያ ስምምነቱ የውሃ ፕሮጀክት ስራዎችና የኤልክትሮ-ሜካኒካል መሰረተ-ልማቶችን የተመለከተ ሲሆን ከጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ኩባንያ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ በልሰቲ አማኑ እና ከቴክኖሎጂ ኢንሰቲትዩቱ የኢንስቲትዩቱ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ሰይፉ አድማሱ ተቋማቱን ወክለው ተፈራርመዋል፡፡
በጋራ ለመስራት ስምምነት ከተደረሰባቸው ተግባራት ጥቂቶቹ፥
- በጥናትና ምርምር
- በማማከር አገልግሎት
- በማህበረሰብ አገልግሎት
- በኮንስትራክሽን ዘርፍ
- በኤሌክትሮ መከኒካል ዘርፍ
- በአጫጭርና ርጅም ጊዜ ሥልጠናዎች
- በኢንተርንሽፕና፣ በመሳሰሉት ዘርፎች በጋራ ለመስራት የስምምነት ፊርማ ትከሂዷል።
በፊርማ ስነስርዓቱ ወቅት አቶ በልስቲ አማኑ ኩባንያችን ከዩኒቨርሲቲው ጋር የተለያዩ የውሃና የኤለክትሮ-ሜካኒካል ስራዎችን እንደሰራ አስታውሰው ይህ ስምምነት መደበኛ የሆነ ግንኙነትን እንዲፈጠር ያስችላል።” ብለዋል፡፡ዶ/ር ሰይፉ አድማሱ በበኩላቸው ተቋማዊ ግንኙነቶች ማህበረሰብን በግባቡ ለማገልግል የሚያስችሉ እንደሆኑ ጠቁመው ተቋማትን አስተባብሮ በጋራ መስራትና ከተቋማት ጋር ግንኙነቶችን መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ የኩባንያችን እቅድና አሰራር ማሻሻያ አገልግሎት ኃላፊ አቶ ጎሸ ሞሳና በባህርዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩተ የሲቪልና የውሃ ሃብቶች ምህንድስና ፋኩልቲ ዲን ዶ/ር ምትኩ ዳምጤም ተገኝተዋል፡፡