የጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ኩባንያ እና የባህርዳር ቴክኖሎጂ ኢስቲትዩት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ::

በጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ኃ.የተ. የግል ኩባንያ እና በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንሰቲትዩት መካከል በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈርሟል፡፡ የመግባቢያ ስምምነቱ የውሃ ፕሮጀክት ስራዎችና የኤልክትሮ-ሜካኒካል መሰረተ-ልማቶችን የተመለከተ ሲሆን ከጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ኩባንያ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ በልሰቲ አማኑ እና ከቴክኖሎጂ ኢንሰቲትዩቱ የኢንስቲትዩቱ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ሰይፉ አድማሱ ተቋማቱን ወክለው ተፈራርመዋል፡፡

በጋራ ለመስራት ስምምነት ከተደረሰባቸው ተግባራት ጥቂቶቹ፥

  • በጥናትና ምርምር
  • በማማከር አገልግሎት
  • በማህበረሰብ አገልግሎት
  • በኮንስትራክሽን ዘርፍ
  • በኤሌክትሮ መከኒካል ዘርፍ
  • በአጫጭርና ርጅም ጊዜ ሥልጠናዎች
  • በኢንተርንሽፕና፣ በመሳሰሉት ዘርፎች በጋራ ለመስራት የስምምነት ፊርማ ትከሂዷል።

በፊርማ ስነስርዓቱ ወቅት አቶ በልስቲ አማኑ ኩባንያችን ከዩኒቨርሲቲው ጋር የተለያዩ የውሃና የኤለክትሮ-ሜካኒካል ስራዎችን እንደሰራ አስታውሰው ይህ ስምምነት መደበኛ የሆነ ግንኙነትን እንዲፈጠር ያስችላል።” ብለዋል፡፡ዶ/ር ሰይፉ አድማሱ በበኩላቸው ተቋማዊ ግንኙነቶች ማህበረሰብን በግባቡ ለማገልግል የሚያስችሉ እንደሆኑ ጠቁመው ተቋማትን አስተባብሮ በጋራ መስራትና ከተቋማት ጋር ግንኙነቶችን መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ የኩባንያችን እቅድና አሰራር ማሻሻያ አገልግሎት ኃላፊ አቶ ጎሸ ሞሳና በባህርዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩተ የሲቪልና የውሃ ሃብቶች ምህንድስና ፋኩልቲ ዲን ዶ/ር ምትኩ ዳምጤም ተገኝተዋል፡፡



Leave a Reply