5 የመስኖ ግንባታ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነዋል።

በ2013 በጀት ዓመት በኩባንያችን በመገንባት ላይ ከነበሩት 7 የመስኖ ግንባታ ፕሮጀክቶች መካከል 5ቱ ተጠናቀው ለአገልግሎት ተዘጋጅተዋል።

እነዚህ ፕሮጀክቶች፥-

  • በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ የቡርቃ መስኖ ግንባታ ፕሮጀክት፣
  • በደሴ ዙሪያ ወረዳ የየጀርቲ መስኖ ግንባታ ፕሮጀክት፣
  • በመሃል ሳይንት ወረዳ የማየስ 1 ፕሮጀክት፣
  • በመሃል ሳይንት ወረዳ ማየስ 2 መስኖ ግንባታ ፕሮጀክት እና
  • በምስራቅ ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ ወረዳ የአዟሪ 1 መስኖ ግንባታ ፕሮጀክት

በበጀት ዓመቱ ተጠናቀው ለአገልግሎት የተዘጋጁና አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ ፕሮጀክቶች ናቸው።በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምዕራብ በለሳ ወረዳ የሆጣ መስኖ ግንባታ ፕሮጀክት እና በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር የወርቄ መስኖ ግንባታ ፕሮጀክቶች በነበረው የስሚንቶ አቅርቦት እጥረት እና ከሚሲ አካባቢ ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ማጠናቀቅ ያልተቻለ ሲሆን በቀጣይ በልዩ ትኩረት ለማጠናቀቅ የሚሰራ ይሆናል።Leave a Reply